የ72 ሰዓት ጊዜው ገደብ ሲያበቃ የአፍሪካ ህብረት ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ አመሩ

ሬውተር እንደዘገበው

ሶስት የአፍሪካ ህብረት ልዑካን – የቀድሞው ፕሬዚዳንቶች የሞዛምቢክ ጆአኪም ቺሳኖ ፣ የላይቤሪያው ኤሌን ጆንሰን ሰርሊፍ እና የደቡብ አፍሪካው ክጋለማ ሞትንታ – ለስብሰባዎች ረቡዕ ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ መግባታቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል ፡፡  በዶ/ር ዐቢይ የተሰጠው የ72 ሰዓታት እጅ የመስጠት ገደብ ከመድረሱ ጥቂት ሰዓታት በፊት አዲስ አበባ የገቡት ልዑካን ተልዕኮ የመብት ተሟጋቾች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዜጎችን ሕይወት ሊያጠፋ ይችላል ያሉትን ስጋት ለማጥፋት ሰላም እንዲመጣ ለመማጠን እንደሆነ ታውቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ መንግሥት የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሃት) መሣሪያውን አስቀምጦ እጅ እንዲሰጥ እሁድ ዕለት የ 72 ሰዓት የጊዜ ገደብ መስጠቱ ይታወቃል።

ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳስታወቀው ሁለቱም ወገኖች ሲቪሎችን አደጋ ላይ ከመጣል መቆጠብ አለባቸው ፡፡ የመንግስት ማስጠንቀቂያ “በከተሞች ውስጥ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያካሂዱ ሲቪሎችን ለመጠበቅ የማያቋርጥ ጥንቃቄ የማድረግ ግዴታውን” አላወገደውም

ሂዩማን ራይትስ ዎች  ሁለቱም ወገኖች ሲቪሎችን አደጋ ላይ ከመጣል መቆጠብ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡ መንግስት በከተሞች ውስጥ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያካሂዱ ሲቪሎችን ለመጠበቅ የማያቋርጥ ጥንቃቄ ይደረጋል ቢልም ሕወሃት ጦሩን ከፍተኛ ቁጥር ህዝብ ብዛት ባለባቸው አካባቢዎች ማስማራቱ ሰለታወቀ ሊከሰት የሚችለውን ዕልቂት መገመት ያስቸግራል በማለት ዘገባዎች ያሳስባሉ።

በፕሬዚዳንት ኦባማ ፕሬዚዳንትነት ወቅት የብሔራዊ ሴኪውሪቲ ካውንስል የአፍሪካ ጉዳይ የቀድሞው ከፍተኛ ዳይሬክተር የሆኑት ግራንት ሃሪስ “የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን የአገር ውስጥ ችግር እና የወንጀል ሁኔታ አድርጎ ስላቀረበው ሉዓላዊ በሆኑ አገሮች ጉዳይ የዲፕሎማሲ እና የአለም አቀፍ የሽምግልና ጥረቶች ለማድርግ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅሰዋል ፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ጆ ቢደን የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሆነው የተሾሙት ጃክ ሱሊቫን ችግሩን ለመፍታት ውይይት እንዲካሄድ አሳስበዋል ፡፡ በኢትዮጵያ መቐለ ዙሪያ ሊደረግ በታሰበው ውጊያ የጦር ወንጀሎችን ጨምሮ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰው ዕልቂት በጣም ስለሚያስጋ  በጣም ያሳስበኛል በማለት በትዊተር ገፃችው አስፍረዋል።

Leave a Reply

%d bloggers like this: