በአትላንታ የ2012 የመስቀል ደመራ አስር ቤተክርስቲያናት በጋራ አከበሩ

ባለፈው ዓርብ መስከርም 16 ቀን 2012 በቅዱስ ሲኖዶስ ስር በደቡብ ምስራቅ አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህገረ ስብከት በአትላንታና አካባቢው የሚገኙ አስር ቤተክርስቲያናት የ2012 የመስቀል ደመራን በዓል በደመቅ ሁኔታ በጋራ አከበሩ። ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የድቡብ ምሥራቅ ሀገር ስብከት ሊቀጳጳስና የሃገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቢ አዲስ ይልማ ቸርነትና የአስሩ አድባራት አለቆች፤ ካህናት፤ ዲያቆናትና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናን የታደሙበት ታላቅ በዓል ፍቅርና አንድነት የታየበት መሆኑን ከቦታው በመገኘት ለማየት ችለናል። ይህንኑ በዕስል በተመለከት የዘገብነውን ቪዲዎ እንድትመለከቱ እየጋበዝን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ እንላለን።

Leave a Reply

%d bloggers like this: