የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ 2020 ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ተብሎ ተሸለመ።

በአፍሪካ በትልቅነቱ የሚታወቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ 2020 ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ በመሆን የ2020 የንግድ ሥራ ተጓዥ ሽልማት (Business Traveller Award) አሸናፊ ሆነ ፡፡

ሽልማቱን በቅርቡ ይፋ የተደረገው ፓናሳ ሚዲያ (Panacea Media) በተሰኘው የንግድ ሥራ ተጓዥ መጽሔት (Business Traveler Magazine)  አዘጋጆች እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ይህ ሽልማት የሚወሰነው የንግድ ሥራ ተጓዥ መጽሔት (Business Traveler Magazine) አንባቢዎች በሚሰጡት ድምጽ ሆኖ የገበያዎችን ውጤት ልኬት በማረጋገጥ የሚታወቅ ገለልተኛ በሆነ የምርመርና ጥናት ኩባንያ ተርጋግጦ ነው።

ሽልማቱ በመደበኛ የሚወሰነው በዓመት ውስጥ ባሉት 12 ወራት የአንባቢያንን ልምዶች በማየት ቢሆንም ዘንድሮ በንግድ ጉዞ ላይ በአብዛኞች አገሮች  ሰፊ ገደቦች የተደረገባችውን ከመጋቢት በፊት ያሉትን ጊዜዎች ሳያካትት ከኤፕሪል እስከ ሐምሌ 2020 በተደረገው የዳሰሳ ጥናት  እንደሆነ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ በመባል ያሸነፈው   ሌሎች ታዋቂ የሆኑ የደቡብ አፍሪካውን SAA፤  የሞሮኮውን ሮያል ኤር ማሮክ (Royal Air Maroc)ና የኬንያውን አየር መንገድ (Kenya Airways) በመቅድም ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ከሌሎች ምርጥ አየር መንገዶች ማለትም ከምርጥ እስያ አየር መንገድ ፤  ከምርጥ ካቢን ሠራተኞች ሽልማት ካገኙት ከሲንጋፖር አየር መንገድ ፤ ምርጥ የአውሮፕላን ጉዞ መዝናኛ ካለው ከኤሜሬትስ አየር መንገድ፣ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል ካለው ከቪርጂን አትላንቲክ (Virgin Atlantic ) አየር መንገድ  እና ምርጥ የዝቅተኛ ዋጋ ይሚታውቅው ኢዚ ጄት (Easy Jet)፤ ምርጥ የሰሜን አሜሪካ አየር መንገድ ዴልታ (Delta) እና ምርጥ የምስራቅ አውሮፓ አየር መንገድ ኤሮፍሎት (Aeroflot) ጎን እንዲሆን ይህ ሽልማት ሊያበቃው ችሏል።

Leave a Reply

%d bloggers like this: