በምሥራቅ አፍሪካ በጎርፍ መጥለቅለቅና፣ በመሬት መንሸራተት 3.6 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ለአደጋ መጋለጡ ተገለጸ።

ከባድ ዝናብ የፈጠረው ችግር ፒቦር በተባለ የደቡብ ሱዳን ከተማ (ፎቶ ምንጭ ሮይተርስ)

ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ በመላው ምስራቅ አፍሪካ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተቀሰቀሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት ናዳ ቢያንስ 3.6 ሚሊዮን ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ አገልግሎት ድርጅት  ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል ፡፡የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (OCHA) “በኬንያ እና በኡጋንዳ የበርካታ ሐይቆች የውሃ መጠን የጨመረ ሲሆን ይህም በሺዎች የሚቆጠሩ ሕዝቦችን ለአደጋ አጋልጧል፡፡

በደቡብ ሱዳን ከሰኔ ወር ጀምሮ 856,000 ያህል ሰዎች ለጎርፍ ተጋልጠዋል ፣ የተፈናቀሉት በግምት 400,000 እንድሚሆኑ  በሪፖርቱ ተካቷል፡፡ በክልሉ ውስጥ ብአሁኑ ወቅት በሕዝቡ ላይ ተጋርጠው ያሉት  ግጭቶች፣ ሁከቶች ፣ የበረሃ አንበጦች እና COVID-19 ላይ ይኸ ተጨምሮ ሕዝቡ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጧል ፣

ሪፖርቱ እንዳመለከተው በኢትዮጵያ 1.1 ሚሊዮን ያህል ሰዎች በጎርፍ የተጠቁ ሲሆን ከ313,000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል ፡፡  ይህ በእንዲህ እንዳለ በኬንያ ከጥቅምት እስከ ዲሴምበር 2019 አካባቢን ያጥለቀለቀው ከፍተኛ የወቅቱን ዝናብ ተከትሎ በርካታ የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች በተለይም ባሪንጎ እና ናይቫሻ የውሃ ደረጃዎች “በታሪክ ከፍተኛ ናቸው” ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል ፡

በተጨማሪም አካባቢው በ2020 በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከቀዬአቸው በመፈናቀላቸው በኑሮ ፣ በትምህርት ቤቶችና በጤና ተቋማት ላይ ተጽዕኖ እንዳሳድር ሪፖርቱ ጠቋሷል።

Leave a Reply

%d bloggers like this: