የኪነት ባለሞያና መምህር መኮንን ገሠሠ በድሮ ተማሪዎቹ ተመሰገነ። (ኢቲቪ)

የኪነት ባለሞያና መምህር መኮንን ገሠሠ በድሮ ተማሪዎቹ ተመሰገነ። (ኢቲቪ)

የኪነት ባለሞያና መምህር መኮንን ገሠሠ ከ32 ዓመታት በኋላ ወደ ውድ አገሩ ሲመለስ 2000 አበሻ በተሰኘ የባህል ቤት በተደረገ ዝግጅት የድሮ ተማሪዎቹና ያሰለጠናቸው የኪነት ባለሞያዎች ፍቅር የተመላበት ከፍተኛ የምስጋና አቀባበል አደረጉለት። 

ኢቲቪ በቦታው ተገኝቶ በመዘገብ በእሁድ ፕራይም ታይም ለእይታ አቅርቦታል።

መኮንን ገሠሠ በአሜሪካ የመጀመሪያዋ የአማርኛ መጽሔት “ላንዳፍታ” መሥራችና ዋና አዘጋጅ እንዲሁም

በአሁኑ ጊዜ አትላንታ የሚገኘው የኢትዮጵያ ላንዳፍታ ሚዲያ ኔትወርክ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ነው።

በአሜሪካ የተወለዱ የኢትዮጵያውያን ልጆች በአጭር ጊዜ የአማርኛ ቋንቋ ማንበብና መጻፍ የሚያስችላችው ሥርዓተ ትምህርት (curriculum) አዘጋጅቶ ያጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ማስተማር የሚጀምር መሆኑ ታውቋል።

Leave a Reply

%d bloggers like this: