- የኪነት ባለሞያና መምህር መኮንን ገሠሠ በድሮ ተማሪዎቹ ተመሰገነ። (ኢቲቪ)
- #ናይ ሓሶት ዜና የብቅዕ – ክፋልን 2 ብትግርኛ
- #ሐስት ዜና ይብቃ – በCNN ዋና መሥሪያ ቤት
- Petition of Eritreans and Ethiopians to GA Senators
- ቃልን በተግባር
- የከሰሩ ወይስ የሰከሩ ፖለቲከኞች?
- 5 ፓርቲዎች ታሪካዊ የጋራ መግለጫ!
- የብፁዕ አባታችን አቡነ ያዕቆብ በረከት – ግብረ ሕማማት
- አቶ ላዕክ ማለደ በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ በቅርቡ በአማራ ቲቪ
- ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው በባክ ግራውንድ ብሪፊንግ (Background Briefing) ሬዲዎ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ
የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላምና የእርቅ ሐዋርያዎች በአትላንታ
August 3, 2019
በአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካቴድራል ከ2016 ዓ.ም. ጀምሮ ሲያወዛግብና ለምዕምናን መከፋፈል ምክንያት ሆኖ የነበረው ጉዳይ በመጨረሻ 18 ነጥቦች በያዘው፤ ግንቦት 22 2011 የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ ድምጽ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል። ውሳኔዎቹ እንደተጠበቁ ሆነው፤ ከአሁን በኋላ ግን በምዕመናን መካከል ያለው የጥል ግድግዳ ፈርሶ ሰላም እንዲመሠረቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ሁለት አባቶችን ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ የሰሜን ወሎ ሀገር ስብከት ረዳት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ቀሲስ በላይ ጸጋዬ የሰላምና የእርቅ ሐዋሪያ አድሮጎ ልኳቸዋል። እኛም ከእነኚህ አባቶች ጋር ያደረግነውን ቃለ ውይይት እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።
ማሳሰቢያ : ችግሩ የጀመረው በ2006 የሚለው በስሁተት ስለሆነ በ2016 ይስተካከል። ይህ ቃል ወይይት የተካሄደው ባለፈው July 25 2019 ስለሆነ ከዚያ በኋላ የሆነውን አይመለከትም።
መልአከ መዊዕ ቀሲስ ሳሙኤል እሸቱ
በአትላንታ ብሥራተ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
ታህሣሥ 2011 የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ላይ
ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በደቡብ ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 11 እዚሁ አገር ተወልደው በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተጠምቀው የድቁና ትምህርት ሲከታተሉ ለከረሙ 11 ወጣቶች የድቁና ማዕረግ ከነሙሉ ክብሩ ሰጡ
August 9, 2019
አትላንታ ከሚገኙ ሶስት አብያት ክርስቲያናት ምናልባትም በስሜን አሜሪካ በጂዎርጂያ 11 እዚሁ አገር ተወልደው በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተጠምቀው የድቁና ትምህርት ሲከታተሉ የከረሙ 11 ወጣቶች ባለፈው እሁድ ጁላይ 14 2019 ስኔልቪል ( Snellville, GA) በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ወደብረጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በደቡብ ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የድቁና ማዕረግ ከነሙሉ ክብሩ መሰጠታቸውን ከቦታው ተገኝተን ለመመልከት በቅተናል።
ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እሁድ ጁላይ 14 2019 ስኔልቪል ( Snellville, GA) በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ወደብረጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተከበረው የቅድሥት ሥላሴ ክብር በዓል ላይ በመገኘትና ሥርዓተ ቅዳሴው ከመሩ በኋላ
1ኛ. ከሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመላከ ምህረት ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን ጌታሁን አቅራቢነት 5 ወጣቶች፤
2ኛ. ከደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመላክ ሰላም ቀሲስ ኤፍሬም
ከበደ አቅራቢነት 2 ወጣቶች፤
3ኛ. ከቅድስት ሥላሴ ወደብረጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ብርሃን በቀሲስ ማንችሎት 4 ወጣቶች አቅራቢነት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አጽድቀው ማዕረጉን በመሰጠት ዲያቆናቱ በየመጡበት አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ መንፈሳዊ መመሪያ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የዲያቆናቱን ወላጆች አመስግነው ዲያቆናቱ ከእንግዲህ ልጅነታቸው የወላጆቻቸው ብቻ ሳይሆን የቤተከርስቲያንቷ እንደሆነ መንፈሳዊ መመሪያ ሰጥተዋል። ደማቅ የሆነውን የማዕረግ አሰጣጥ ሥነሥርዓትና የብፁዕ አቡነ ያዕቆብና መመሪያ ለመስማት የሚከተለውን ቪዲዎ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።